Search

ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሰኞ ሰኔ 08, 2018 424

በባህል ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ኢቢሲ ከወዳጆቹ እንዳረጋገጠው ድምፃዊው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ነው በዛሬው ዕለት ያረፈው።

በባህላዊ ሙዚቃዎቹ ይበልጥ የሚታወቀው ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው፣ ከሙዚቃው ውጭም በትወና ይሳተፍ ነበር። 

ድምፃዊ ሰማኸኝ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

ድምፃዊ ሰማኸኝ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደ አዲስ በክልሎች ሲያካሄድ በነበረው ኢትዮጵያ አይዶል ላይ ዳኛ ሆኖ የጥበብ አጋርነቱን አሳይቷል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።