Search

የኢትዮጵያ አዲስ መልክ እና ትዕምርት:- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ

Aug 13, 2025

በህዝብ አቅም የተሰራው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ሰላም፣ ብርሃን ብሎም አንድነት የሚጠበቅበት መሳሪያ ነው ሲሉ ነው ጥላሁን ኤርዱኖ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) ገለፁ።

ቀድሞ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የነበሩት ዶ/ር ጥላሁን አሁን የአፍሪካ ቀንድ እና መካከለኛው ምሥራቅ ጂኦፖለቲክስ ተመራማሪ ናቸው።

በአባይ ወንዝ ግድብ ግንባታ ዙሪያ "የግብጽና አጋሮቿ ጠላትነት እስከ መቼ?" ወይም "የግድቡ እርሾ" የተሰኘ መጽሐፍም ጽፈዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ለመፍጠር አንድ እርምጃ የሄድንበት ግድቡ በላይኛው እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የነበረውን ሻካራ መስተጋብር ያለሰለሰ መሆኑን ዶ/ር ጥላሁን ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል።

ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ነው የገለፁት።

ሕዳሴ ግድብ በዜጎች ህይወት ውስጥ የዘለቀ ሽግግር መፍጠር የሚቻልበት የለውጥ መሳሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ግድቡ ታዳሽ ካልሆነ ምንጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረትን የሚያስቀር፣ ለማገዶ ይጨፈጨፍ የነበረውን ደን የሚታደግ፣ ለሶላር ግዢ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ የሚቆጥብ መሆኑን አስረድተዋል።

አኗኗራችን ሲቃና አስተሳሰባችን አብሮ መቃናቱ፣ ልማታችን ላይ ስናተኩር ሰላማችንን ማስጠበቅ መቻላችን የአዲስ ምዕራፍ ጅማሮ መሆኑን ይናገራሉ።

ሕዳሴ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ አዲስ መልክ የሚሰጥ ዓርማዋ ነው በማለት ገልፀውታል።

በአፎሚያ ክበበው

#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #GERD