በኬፕ ቬርዴ በሳኦ ቪሴንቴ እና ሳንቶ አንታኦ ደሴቶች ላይ ባጋጠመ ከባድ የጎርፍ አደጋ በደሴቶቹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
በአደጋው እስካሁን የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ከ1 ሺህ 500 በላይ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የነፍስ አድን ሠራተኞች የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ በመሆናቸው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊሻቅብ እንደሚችል ተሰግቷል።
ጎርፉ በመንገዶች፣ ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይም ከባድ ጉዳት አስከትሏል።
በደሴቶቹ በቅድሚያ የተከሰተው ኤሪን የተሰኘ አውሎ ንፋስ ከባድ ዝናብ እንዲከተል ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በ5 ሰዓታት ውስጥ 193 ሚሊሜትር ዝናብ የጣለ ሲሆን፤ ይህም ከሳኦ ቪሴንቴ ዓመታዊው የዝናብ መጠን በእጅጉ የላቀ መሆኑ ነው የተገለፀው።
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦላቮ ኮሪያ ጎርፉን ያልተጠበቀ ከባድ አደጋ ሲሉ ገልፀውታል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #EBCdotstream #capeVerde #floods