የሃይማኖት ተቋማት ተፈጥሯዊ ግብራቸው ሰላምን ማስተማር፣ ሰላምን መገንባት መሆኑን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለፁ።
ሰው በግል፣ በቡድን እና በአመለካከት ሰው ከሰው፣ ሰው ከተፈጥሮ እንዲሁም ሰው ከፈጣሪ ጋር የሚቃረንበት እና የሚጋጭባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ገልፀዋል።
ሰላምን ለማፅናት ሰው መጀመሪያ ከራሱ ጋር ከዚያም ከተፈጥሮ እና ከፈጣሪ ጋር መታረቅ እንዳለበት አንስተዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ሰላምን በምድር ላይ ለማፅናት የፈጣሪ አደራ አለባቸው ካሉ በኋላ፤ ሁሉም የእምነት ተቋማት በትምህርታቸው ያለውን ክፍተት በመሙላት ሰላምን ለማፅናት መሥራት እንዳለባቸው አመላክተዋል።
ሰላምን ለማፅናት በሚደረገው ጥረት እያንዳንዱ ሰው የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ አንስተው፤ "ለአንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላው አድርግ፤ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን በሌላው ላይ አታድርግ" የሚለውን ብሂል መከተል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ሰላም #የሃይማኖትተቋማት