Search

የመደመር አንቀጽ

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 66

በሀገራችን የአለመቻቻል ባህል በነባር ፓራዳይሞች ርዕዮተ ዓለማዊ ጽንፈኝነት ውስጥ ይበልጥ ቅርጽና መልክ ይዞ፤ ለሀገር አሳሳቢ የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

 

በብዙኃኑ ዘንድ የሚታየው የአለመቻቻል ባህልና በፖለቲካ ልሂቁ ዘንድ ያለው ጽንፈኝነትና ዋልታ ረገጥነት በጊዜ ካልታረመ፤  ሀገር አፍራሽ በሆነ የከፋ ድርጊት መገለጡ አይቀርም፡፡ 

ድርጊቱ ማንነትን ወይም ልዩነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሲሆን፤ ብዙኃኑን ሳይሆን ጥቂት የኅብረተሰቡን ክፍልን የሚገልጽ ነው።

የአክራሪነት ጥቃት ጥቂት የኅብረተሰብ ክፍልን የሚገልጽ ቢሆንም፤ ተፅዕኖው ወደ ብዙኃኑ ተዛምቶ አክራሪነት እንዲባባስና ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ጦሱ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ አይቀርም።

የመደመር ትውልድ 

ገጽ - 54