Search

ዘመናትን የተሻገረ የታሪክ ባለቤትነቱ ዛሬም የቀጠለው አየር ኃይላችን

ዓርብ ሰኔ 12, 2018 90

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ለሕዝባዊ ኩራት ዋስትና ሆኖ የቆመ፣ ዘመናትን የተሻገረ የታሪክ እና የጀግንነት ማማ ነው።

"ሰማዩ የኛ ነው" የሚለው የአየር ኃይሉ መሪ ቃል መፈክር ብቻ ሳይሆን፣ በጀግኖች አብራሪዎች ደም እና አጥንት፣ በላቀ የአየር ላይ የበላይነት እንዲሁም ጥልቅ በሆነ የሀገር ፍቅር የተጻፈ እውነት ነው።

አንድ ክፍለ ዘመን የተጠጋ ዕድሜ ያለው የሰማዩ ንስር በአፍሪካ ሰማይ ሥር ያስመዘገበው ደማቅ ታሪክ፣ ሀገራችን ያጋጠሟትን የሕልውና አደጋዎች ሁሉ በድል እንድትወጣ አድርጓል።

በተለያዬ ጊዜ አኩሪ ገድል የፈጸመው አየር ኃይላችን፣ ዛሬ ላይ ዘመኑን የሚመጥን የላቀ አደረጃጀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ደርሷል።

አየር ኃይል 1969 . ወረራ በቁጥር እና በዘመናዊነት የማይመጣጠን ትጥቅ ይዞ፣ F-5E ተዋጊ ጄቶች የጠላትን 25 የጦር አውሮፕላኖች (MiG-17 እና MiG-21) በአየር ላይ በማስቀረት ፍጹም የበላይነትን ተቀዳጅቷል።

በዚህ ውጊያ እንደእነ ብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ተፈራ፣ ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ እና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ያሉ ጀግኖች ታሪክ ሠርተዋል።

1991-1993 . ጦርነት፦ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ Su-27 እና MiG-29 ፊት ለፊት በተፋለሙበት ውጊያ፣ የኢትዮጵያ Su-27 ተዋጊ ጄቶች የጠላትን አውሮፕላኖች እንደ ጉም በማትነን ሀገራችን የማትደፈር መሆኗን ዳግም አረጋግጠዋል።

"ኢትዮጵያ አሁን ሉዓላዊነቷ ላይ ትንኮሳ የሚሰነዝሩ ኃይሎችን በሰማይም ሆነ በምድር አሳድዳ የምትቀጣ ኃይል ሆናለች!" በሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ልክ፣ አየር ኃይሉ የተዋጊ ጄቶቹን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ ወደ 5 ትውልድ (5th Gen) ቴክኖሎጂ ለመሸጋገር በትኩረት እየሠራ ነው።