Search

ብቁ የፖሊስ ሀይል ያዋለደው የፀጥታ ተቋማት ሪፎርም !!

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 41

የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋም ታሪክ ወደ ኋላ ሲቃኝ፣ ጠንካራ እና የተደራጀ የጸጥታ ኃይል ለመገንባት የተደረጉ ትላልቅ ጥረቶችን እናገኛለን።

በተለይም ከጣሊያን ወረራ ማክተም በኋላ በ1934 ዓ.ም ዘመናዊው የፖሊስ ሰራዊት በይፋ ሲመሰረት፣ ተቋሙን በማደራጀት  ረገድ ጥረቶች ተደርገዋል።

ይሁን እንጂ፣ የሀገራችን የፖሊስ እድገት ከዘመን ዘመን አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል። ተቋሙ   በህብረተሰቡ ዘንድ እየገነባ የነበረው ገጽታ እጅግ ፈታኝ እና አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል።

ፖሊስ የህዝብ አገልጋይ፣ የሰላም እና የደህንነት ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በዜጎች ዘንድ እንደ አስፈሪ ኃይል የሚታይበት  ነበር። 

May be an image of text

የሙያ ስነ-ምግባር መጓደል፣ የሰብአዊ መብት አያያዝ ክፍተቶች እና ወንጀልን በባህላዊ መንገድ የመመርመር አዝማሚያ የፖሊስን ውጤታማነት በእጅጉ ይጎዳው ነበር።

ከዚህም ባሻገር በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ተቋሙ ሰፊ ክፍተት ነበረበት።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የታሪክ እና የአሰራር ግድፈት ለማረም፣ እንዲሁም የፍትህ እና የጸጥታ ተቋማትን ከመሰረቱ ለማነጽ የጀመረው ጥልቅ የሪፎርም ሂደት ይህንን ገፅታና ታሪክ በሚገርም ፍጥነት ቀይሮታል።

መንግስት በወሰደው ቆራጥ እርምጃ የነበሩትን መዋቅራዊ ድክመቶች በማረም አሁን ላይ እጅግ የላቀ  ፕሮፌሽናል የሆነ የፖሊስ ሃይል መፍጠር ተችሏል።

No photo description available.

የተቋማት ሪፎርሙ የፌደራል ፖሊስን ገጽታ በማደስ፣ ተቋሙን ወደ ቀደመ ታሪካዊ ክብሩ በመመለስ የህዝብ እውነተኛ አለኝታ ማድረግ ችሏል።

የዛሬው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባል በከፍተኛ ደረጃ በዲሲፕሊን የታነጸ፣ የላቀ የሙያ ስነ-ምግባርን የተላበሰ እና ህዝብን በአክብሮት የሚያገለግል ነው።

አዲሱ የፖሊስ ሃይል  ለህገ-መንግስቱ እና ለህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ፍጹም ታማኝ የሆነ  እና ሙያውን ከልብ የሚወድ ኃይል ሆኖ ተገንብቷል።

ከምንም በላይ ደግሞ የአሁኑ የፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ እጅግ የተራቀቀ ሆኗል።

በጥቂት የዓለማችን ባደጉ አገራት ብቻ የሚታየውን  ከፍተኛ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ የዲጂታል መረጃ ትንተና አቅሞችን በመጠቀም ወንጀልን የመከላከል እና የመቆጣጠር ብቃቱን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል።

ዘመናዊ የፎረንሲክ ላቦራቶሪዎች እና የደህንነት መቆጣጠሪያ ማዕከላት በቴክኖሎጂ የታገዙ በመሆናቸው፣ ወንጀለኞች ከህግ ማምለጥ የማይችሉበት አስተማማኝ አውታር ተዘርግቷል።

በአጠቃላይ ደረጃ፣ ኢትዮጵያ በፌደራል ፖሊስ ላይ ያካሄደችው ይህ የተሳካ ሪፎርም  የሃገር መንግስት ግንባታን (State Building) መሰረት በእጅጉ የሚያጠነክር ነው።

የፖሊሳዊ ልምድና ክህሎትን  ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ጋር በማዋሃድ፣ ጠንካራ እና በህዝብ አመኔታ የተገነባ የጸጥታ ተቋም መፍጠር ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና ለዘላቂ ተቋማት ግንባታ (Institution Building) የማይተካ ሚና አለው።

ይህ ዘመናዊ እና ፕሮፌሽናል የፖሊስ ሃይል የዜጎችን ሰላም በማስጠበቅ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በማፋጠን ረገድ ጠንካራ የጀርባ አጥንት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።