Search

ከዘመናዊ የበረራ ሥልጠና እስከ አስተማማኝ የውጊያ አቅም

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 46

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ የመሆን ታላቅ ራዕዩን ለማሳካት በከፍተኛ ትጋት እየተንቀሳቀሰ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የ3ኛው አየር ምድብ በሰው ኃይል ማብቃት፣ በቴክኖሎጂ ዝግጁነትና በውጊያ መሠረተ ልማት ግንባታ እያስመዘገበ ያለው ስኬት ለተቋሙ ራዕይ መሳካት እንደ ጽኑ መሠረት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

May be an image of aircraft, offroad vehicle and text

የአየር ምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ እንደገለጹት፤ ምድቡ በአሁኑ ወቅት ዘመናዊውን ግሮብ 120ቲፒ የበረራ ሥልጠና አውሮፕላን ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ምጥቀት ጋር አዋህዶ በጥበብ እየዘመነ ተልዕኮን እየተወጣ ይገኛል።

በዚህም የሀገር ውስጥ አብራሪዎችን ከማሰልጠን ባለፈ፣ የውጭ ሀገራት ዜጎችን ጭምር ተቀብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያበቃ ሲሆን፤ ይህም ተቋሙን የቀጣናው የሥልጠና ማዕከል በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ዘመናዊ ሥልጠና የፓይለቶችን የክህሎት የበላይነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ በማንኛውም ውስብስብ የበረራ ግዳጅ ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ የሰማይ ላይ ጀግኖችን በኢትዮጵያ ለማፍራት ማስቻሉን አክለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የቴክኒክና የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም በማከናወንና ትጥቆችን ለተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ የውጊያ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ስኬት ተመዝግቧል።

በአየር ምድቡ የሠራዊቱን ሞራልና ዝግጁነት ለማረጋገጥ እንዲቻል፣ ደረጃቸውን የጠበቁና ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።

May be an image of aircraft

ይህም አባላቱ በሥራቸው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉና ግዳጃቸውን በሙሉ አቅም እንዲወጡ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

በሌላ በኩል የጠላትን ኃይል በመደምሰስ ረገድ ምድቡ በታጠቃቸው ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ላይ የተፈጠረው የኦፕሬሽንና የታክቲክ ብቃት በከፍተኛ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አዛዡ አብራርተዋል።

ይህም ማለት በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በጠንካራ የውጊያ መሠረተ ልማት መካከል የተፈጠረው ጥምረት፤ አየር ምድቡ በማንኛውም ወቅትና ቀጣናዊ ሁኔታ ውስጥ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በድል ለመወጣት ሙሉ ዝግጁነት ላይ መሆኑን ቀማረጋገጡን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማሕበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል።