በ23ኛው ዓለም ዋንጫ መጀመር አስቀድሞ "አፍን ሸፍኖ ማውራት" በቀይ ካርድ ከሜዳ እንደሚያሰናብት የሚገልፅ አዲስ ህግ ይፋ ሆኖ ነበር።
በዓለም ዋንጫው በቱርክዬ እና በፓራጓይ መካከል በተካሄደው ጨዋታ የፓራጓዩ ሚጉዌል አልሚሮን የቱርኪዬውን መርት ሙልዱርን አፉን ሸፍኖ በተከለከለው መንገድ ማነጋገሩ፤ በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (VAR) በመረጋገጡ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በዓለም ዋንጫ የምድብ 4 ሁለተኛ ጨዋታ ቱርኪዬን የገጠመችው ፓራጓይ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፋለች።
ማቲያስ ጋላርዛ የውድድሩን ፈጣን ግብ 64ኛው ሴኮንድ ላይ አስቆጥሮ ፓራጓይን አሸናፊ አድርጓል። ቱርኪዬ መሸነፏን ተከትሎ ከምድቡ ተሰናብታለች።