Search

የኩላሊት እጥበት ህክምና በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 53

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ህክምና አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

May be an image of one or more people, dais and text

በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ ዶ/ር ደረጀ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ይህ ማዕከል ከመከፈቱ አስቀድሞ የምረዛ ታካሚዎችን የተሟላ ሕክምና ለመስጠትም ሆነ በድንገተኛና በከባድ የኩላሊት ሕመም ለሚሰቃዩ ህሙማን ሙሉ ድጋፍ ማድረግ አለመቻሉን ጠቁመው በዚህም ምክንያት ታካሚዎች ወደ ሌላ ቦታ ሪፈር ያደርግ ነበር ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው አራት ዘመናዊ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ማሽኖችን ማስገባቱም ተገልጿል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በቅርብ ጊዜ ወደ ሁለንተናዊ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (Comprehensive Specialized Hospital) ለማሸጋገር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም ነው የተጠቆመው።

የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ህክምና ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ለኢትዮጵያ የኩላሊት ማኅበር፤ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ለሆስፒታሉ አመራሮች፤ ለባለሙያዎችና ለሠራተኞች ምስጋና ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: