ዛሬ ላይ የተለያዩ ትላልቅ ሚዲያዎች ይበልጥ ተደራሽ ከሚሆኑባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል የሞባይል መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽኖች) ይገኙባቸዋል።
እነዚህ መተግበሪያዎች የሚመረጡበት ምክንያት ሰዎች በየትም ቦታ ሆነው ዜናዎችን፣ የቀጥታ ሥርጭቶችን እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ለመከታተል የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንም (ኢቢሲ) ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ በራሱ አቅም የሞባይል መተግበሪያ አበልጽጎ በሥራ ላይ አውሏል።
መተግበሪያው የተለያዩ ይዘቶችን በውስጡ ያካተተ በመሆኑ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዜናዎችን፣ የጤና እና የቴክኖሎጂ መረጃዎችን በተለያየ አማራጭ ለማቅረብ የሚያስችል ነው።
እንዲሁም የረሠመዝናኛ፣ ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎች በሚኖሩበት ጊዜ በፍጥነት ያደርሳል።
ሳይከታተሏቸው ያለፉ ፕሮግራሞችንም ወደኋላ መለስ ብለው መመልከት የሚችሉበት አፕሊኬሽን ነው።
ኢቢሲ ከዘመኑ ጋር ዘምኗል! በየትኛውም ቦታ መረጃን በኪስዎ እንዲያገኙ አስችሏል!
መተግበሪያዎቹን ከአፕ ስቶር እና ፕለይ ስቶር አውርደው ዲጂታል ኢቢሲን ይቀላቀሉ።
አንድሮይድ (Android) ስልክ የምትጠቀሙ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/6KegY
አይኦኤስ (iOS) ስልክ የምትጠቀሙ ደግሞ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/hFuA1
#EBC #ebcdotstream #Digital_EBC #DigitalEthiopia #EBCApp