Search

ኢትዮጵያ ዕድገቷ ራሱን ችሎ የሚቀጥልና ለውጥ የሚያመጣበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት እየገነባች ትገኛለች - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ሰኔ 16, 2018 43

ኢትዮጵያ ዕድገቷ ራሱን ችሎ የሚቀጥልና ለውጥ የሚያመጣበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት እየገነባች እንደምትገኝ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (/) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በተገኙበት ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር በሚል መሪ ሐሳብ ኢትዮጵያ ታከናውናለች ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ብሩክ ታዬ (/) በዚሁ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ ለዘመናት ከዘለቀው ሀገራዊ ትልም ተነሥቶ አሁን ላይ በትጉህና ግልጽ መርሆዎች እንዲሁም በተዋቀረ አፈጻጸም ወደሚመራ የለውጥ ዘመን መሸጋገሩን አመልክተዋል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ የለውጡ መንግሥት ሀገራዊ ተስፋን ከተቋማዊ አቅም ጋር ወደሚያጣጥም፣ ይበልጥ አመቺ፣ ቅደም ተከተላዊ እና የፋይናንስ ሥነ-ሥርዓትን ወደ ተከተለ አካሄድ ቁርጠኛ ሽግግር ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህም መሠረተ ልማትን ወደ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ እሴት እና ለትውልድ ተሻጋሪ ሀብት እንዲቀየር እያደረገው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የንጹሕ ኢነርጂ፣ የዲጂታል ማስፋፊያ፣ የትራንስፖርት፣ የኮንስትራክሽን እና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሀገሪቱ የምታደርገውን የለውጥና የብልጽግና ጉዞ እየመሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ዕድገቷ ራሱን ችሎ የሚቀጥልና ለውጥ የሚያመጣበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት እየገነባች ትገኛለች ሲሉም ጠቁመዋል።