Search

ሶማሊ ክልልን ይበልጥ በልማት ያለመ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ

ሓሙስ ነሐሴ 08, 2017 140

በሶማሊ ክልል የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የልማት ስራዎችን ለማጎልበት ያለመ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በውይይቱ ላይ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተደሰድር ሙስጠፋ ሙሁመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በአዲስ አበባ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።

ባለፉት 7 ዓመታት በክልሉ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው በመድረኩ ተገለጿል።

 

 

የውይይት መድረኩ በተለይ ከክልሉ ውጪ የሚገኙ ተወላጆች እየተከናወኑ በሚገኙ የሰላም ፣የልማት እና የመልካም አስተዳድር ሥራዎች ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማላቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ባለፉት 7 ዓመታት በሶማሊ ክልል በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተካሂዷል።

 

 

በቴዎድሮስ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: