የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎች ጥራት እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የላብራቶሪ ምርመራ ሥራዎቹን ይፋ አድርጓል።
ባለሥልጣኑ በጉዳዩ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር እና የመስክ ምልከታ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱንም አስታውቋል።
የሕብረተሰቡን ጤና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሕክምና ግብዓቶች ጥራት እና ፈዋሽነት ቀዳሚው ተግባር መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡
የተዘጋጀው መርሐ ግብር ጥራቱን ያልጠበቀ እና ሀሰተኛ መድኃኒት ወደ ሕብረተሰቡ እንዳይደርስ የሚያደርገውን የቁጥጥር ሥርዓት ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አስታውቋል።
ባለሥልጣኑ አሁን የጀመረው ይፋዊ የምክክር እና የመስክ ምልከታ መርሐ ግብር የቁጥጥር ሥርዓቱን ዘመናዊነት የሚያሳይ ነው።
ይህም በሀገራችን የጤናው ዘርፍ ላይ የሚታየውን የአቅርቦት ጥራት ችግር ለመቅረፍና በሕክምና መሣሪያዎች ላይ ያለውን ጥብቅ ቁጥጥር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።
በቶክ ሮች