Search

ሀገራዊ ምክክሩ ከጥርጣሬ ወደ መተማመን እና ተስፋ የሚያሸጋግረን ታላቅ ብሔራዊ ሁነት ነው

ሰኞ ሰኔ 22, 2018 60

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ውይይት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊ እና የተረጋጋች ሀገርን ለማስረከብ የሚደረግ ታሪካዊ የይቅርታና የመግባባት ጉዞ ነው።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ያሳለፈቻቸውን የተዛቡ ትርክቶች እና የፖለቲካ ቁርሾዎች በውይይት መፍታት ትውልዱ ከጥላቻ ፖለቲካ ወጥቶ በጋራ እሴቶች ላይ እንዲታነጽ ያስችላል።

ይህ ሂደት ትውልዱ በጋራ መግባባት ላይ የተገነባ አስተማማኝ መሠረት እንዲኖረው ከማድረጉ ባሻገር የውይይት ባህልን እንዲያዳብር የሚያስችለው ነው።

ወጣቱ ትውልድ ጉልበቱን ለግጭት ሳይሆን ለፈጠራ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እና ለሳይንሳዊ ዕድገት እንዲያውል ዕድል ይፈጥራል።

በተጨማሪም ምክክሩ በሁሉም ዘንድ በጋራ እሴቶች ላይ የተመሠረተ የሀገር ባለቤትነት ስሜትን በመፍጠር ብሔራዊ የጋራ ሕልም ቀርጾ በጋራ ለመተግበር ያስችላል።

በሕዝቦች መካከል የጋራ መግባባት መፈጠሩ የዜግነት ክብርን ከማሳደጉም በላይ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ተሰባስቦ ለሀገራዊ ዕድገት የሚተጋ ትውልድ ይፈጥራል።

በጥቅሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ትውልዱን ከክፍፍል ወደ አንድነት፣ ከጥርጣሬ ወደ መተማመን እና ተስፋ የሚያሸጋግር ታላቅ ብሔራዊ ሁነት ነው።

በሃና ምንዳሁን