Search

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ (ሰኔ 23) ይጀምራል

ሰኞ ሰኔ 22, 2018 94

2018 የትምህርት ዘመን 12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 . በመላ ሀገራችን 607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ለፈተናው በድምሩ 563 ሺህ 501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257 ሺህ 45 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁን እና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል።

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (Admission Card) የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም።

ፈተናው በበይነ መረብ 6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 . እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ፣ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባር እና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።