Search

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ለዓለም የማስተዋወቅ መርኃ ግብር

ሓሙስ ነሐሴ 08, 2017 112

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን ለዓለም የማስተዋወቅ መርኃ ግብር በስምንት ሀገራት እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡

2ኛው ዙር የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ዓለም አቀፍ ችግኝ ተከላ (plant fraternity) ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሂዷል።

በስምንት አገራት የሚደረገው መርኃ ግብር ዓላማ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ልምድ ለዓለም ማካፈል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በነገው ዕለትም የኢትዮጵያ ወጣቶች ልዑካን ወደ ፓኪስታን ሀገር በቀል ችግኞችን ይዘው የሚጓዙ ይሆናል፡፡

መርኃ ግብሩ በኢትዮጵያና በስምንቱ አገራት በሚገኙ የመጪው ትውልድ መካከል ህዝባዊ መሠረት ማጽናት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

መርኃ ግብሩ በብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የተዘጋጀ ነው፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ታደሰ፤ መርኃ ግብሩ የህዝብ ለህዝብ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ፤ የኢትዮጵያ ልኩካን በአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ለፓኪስታን በማካፈል በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

በአባዲ ወይናይ

#EBC #EBCdotstream #GreenLegacy #ProsperityParty