ክረምትና በጋ ብለን የአየር ሁኔታው የሚለያይባቸውን ጊዜያት እንደምንከፍለው ሁሉ፤ የአንድ ትወልድ ወቅት፡ ክሥተቶች የሚከሠቱባቸውን ጊዜያት የሚገልጽ ነው፡፡
የሰዎች የክረምትና የበጋ የአኗኗር ዘዬና ቅርጽ የተለያየ ነው፡፡ ለክረምት ዣንጥላ በመያዝ፣ ጃኬት በመደረብ እና የሚያሞቃቸውን ልብስና ምግብ በመጠቀም ብርዱን ያሳልፋሉ።
ቀለል ያሉ ልብሶችና የሚያቀዝቅዙ አማራጮች ደግሞ ለበጋው ሙቀት ምላሽ የሚሰጡበት መንገድ ሆኖ ያገለግላል።
ከትውልድ ትውልድ እንደተወለዱበትና እንዳደጉበት የተለያዩ ወቅቶች፤ የሚያጋጥማቸው ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ክሥተታዊና ሂደታዊ ለውጥም፡ እንዲሁ የተለያየ አመለካከት፣ ባህሪና ልማድ እንዲኖራቸው ያደርጋል።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 13/14