Search

ከታሪክ ገፅታ ባሻገር የቱሪዝም የጎላ አስተዋጽኦ

ረቡዕ ሰኔ 24, 2018 58

ቱሪዝም ያለፈውን ታሪክና ቅርሶችን ለዓለም ከማሳየት ባለፈ የሀገራዊ ዕድገት ጉዞን የሚያፋጥኑ በርካታ አንቀሳቃሽ ሞተሮችን በውስጡ የያዘ ግዙፍ ኢንዱስትሪ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) “ኢትዮጵያ አንድ ቪዛ፣ ዓለም በውስጧበሚል መሪ ሐሳብ ባደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ ላይ እንዳመለከቱት፣ የቱሪዝም ዘርፍ የሀገረ መንግሥቱን ትረካ በመቀየርና አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ቱሪዝምን ከባህላዊው አቀራረብ አውጥቶ ከዘመናዊው የልማት ሥራዎች ጋር ማስተሳሰር መቻሉ ዘርፉ ለሀገር የሚያበረክተውን ዘላቂ ጥቅም ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።

የዚህ አዲስ የቱሪዝም ዕይታ ዋነኛው መገለጫ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን መፍጠሩ ላይ ነው።

አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች፣ ፓርኮችና የልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የኑሮ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል።

ይህም ቱሪዝም የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ የድህነት ቅነሳ ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን ያረጋግጣል።

የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስፋፋት ሥራ ከከተማ ውበት ማሳደግና ከኮሪደር ልማት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለከተማ ፅዳት የተሰጠው ልዩ ትኩረት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጎብኝዎች ደግሞ ማራኪና ሳቢ እንድትሆን አድርጓታል።

ከዚህም በላይ ቱሪዝም የኢትዮጵያን ገፅታ በመቀየር እና በመገንባት ረገድ ጠንካራ የዲፕሎማሲ አውታር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ መዳረሻቸውን ሲያደርጉም ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው የተዛባ አመለካከት እንዲቀየር በማድረግ ረገድ ከዲፕሎማሲ ሥራ በላይ የጎላ ሚና ይጫወታል።

በሃና ምንዳሁን