Search

አዋሽ ባንክ ከታክስ በፊት 40.7 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ረቡዕ ሰኔ 24, 2018 54

አዋሽ ባንክ 2025/2026 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 40 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው በሰጡት መግለጫ፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ በካፒታል ገበያ ተመዝግቦ ወደ ሥራ መግባቱ ካሳካቸው ግቦች መካከል ቀዳሚ መሆኑን ገልጸዋል።

ባንኩ በበበጀት ዓመቱ 25 ተጨማሪ ቅርጫፎችን መክፈቱንና በዲጂታል ዘርፍም ራሱን ማዘመኑን ተናግረዋል።

አዋሽ ባንክ ከታክስ በፊት ያልተጣራ 40.7 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ካፒታሉን 10.6 ቢሊዮን ማሳደጉንም አመልክተዋል።

ባንኩ 467.8 ቢሊዮን ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለው ገልጸው፣ 53 ቢሊዮን ብድር በመደበኛ የብድር አገልግሎት እንዲሁም 2.6 ቢሊዮን በላይ ብድር በዲጂታል መንገድ ለደንበኞች መስጠቱን ጠቁመዋል።

2 በመቶ በላይ የተበላሸ የብድር መጠን በዓመቱ ያስመዘገበው ባንኩ፣ 2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪን መሰብሰቡም ተገልጿል።

አዋሽ ባንክ በቀጣይ ዓመት በጎረቤት ሀገራት ቅርጫፎችን ከፍቶ ለመሥራት ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃድ እስኪያገኝ እየተጠባበቀ እንደሚገኝም በዚሁ ወቅት አስታውቋል።

በኤዶም አማረ