Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ፣ ሊዮ በረራ ጀመረ

ረቡዕ ሰኔ 24, 2018 50

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያካሄደው ባለው የኔትዎርክ ማስፋፊያ ወደ ፈረንሳይ፣ ሊዮ አዲስ የበረራ አገልግሎት ጀምሯል።

የሊዮ በረራ መጀመሩን ተከትሎ አየር መንገዱ በፈረንሳይ ያሉትን መዳረሻዎች ወደ 3 አሳድጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሳው በሰጡት መግለጫ፣ የሊዮ በረራ በአፍሪካ እና በፈረንሳይ መካከል ያለውን የንግድ፣ የቱሪዝም እና የባህል ትስስር ለማጠናከር ታስቦ የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል።

ሊዮ የፈረንሳይ ሁለተኛዋ ትልቅ የኢኮኖሚ ማዕከል እና የኢንዱስትሪ ከተማ በመሆኗ የበረራው መጀመር ወደ ፈረንሳይ ለሚጓዙ ደንበኞች አማራጭ ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይም ወደ 5 ተጨማሪ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች በረራ እንደሚጀምር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር፣ አሌክሲ ላሜክ የሊዮ በረራ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ብለዋል።

በቢታንያ ሲሳይ