የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አሰራር በመለወጥ ምቹ እና ቀልጣፋ አሰራር እንዲከተሉ እየተደረጉ መሆኑን የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ባንቺ አምላክ ገ/ማሪያም ገለጸዋል።
ኃላፊዋ ከኢቲቪ አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ያሉ ሕዝብ አገልጋይ ተቋማት ምቹ እና ቀልጣፋ አሰራር እንዲኖራቸው ለማድረግ፤ የስማርት ሲቲ ግንባታ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑንም ነው ያነሱት።
በአማራ ክልል ቀልጣፋ አሰራርን ለማስኬድ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ቀልጣፋ እና ምቹ አሰራር እየተዘረጋ እንደሆነ አንስተው ገቢዎች ቢሮ ፣ ንግድ ቢሮ እና ወሳኝ ኩነት ለአብነት እንደሚጠቀሱም ጠቁመዋል።
በቀጣይ 10 የሚሆኑ ተቋማትን አሰራር ለማዘመን እና ለሕብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ የታለመ ስለመሆኑም ነው የገለጹት።
ለዲጂታላይዜሽን ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አንስተው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት እና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮን በማቋቋማም ቀልጣፋ አሰራሮችን እየተሰሩ ነው ብለዋል።
የሐረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዚነት ዩሱፍ በበኩላቸው፤ እንደ ሐረሪ ክልል ሕብረተሰቡን ያማረሩ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንደነበሩ አንስተው አገልግሎቶቹን በመለየት ወደ ሥራ መገባቱንም ገልጸዋል።
በዚህም ወደ 13 የሚጠጉ የክልሉ ተቋማት በቴክኖሎጂ በመደገፍ አገልግሎት መስጠት ላይ እንደሚገኙም ነው የጠቀሱት።
በቴክኖሎጂ በመደገፍ የሕብረተሰቡን እንግልት እና ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ስለመሆኑ ነው ኃላፊዋ ጠቁመዋል።
በሜሮን ንብረት