የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፖሊስ ተቋም እየሠራቸው ባሉ የሪፎርም ሥራዎች እና ሠራዊቱ በሕዝብ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ እንዲወጣ የማድረግ ተግባር፣ “የሰራዊቱን መንደር እንገነባለን” ሲል የገባውን ቃል ዛሬ ወደ ተግባር ማሸጋገሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
“እያደገች እና እየዘመነች ከመጣችው የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባን ለሚያገለግል የፖሊስ ሠራዊት የጀመርነው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ባለ 15 ፎቅ የሆኑ 12 ሕንፃዎች ሲሆኑ፤ የሠራዊቱ አባላትን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በመቀነስ በትጋት እና በአግባቡ ሕዝቡን እንዲያገለግል ለማድረግ ነው” ብለዋል ከንቲባዋ።
በኮሚሽኑ በከፍተኛ ትጋት የተጀመሩ የሠራዊቱን አባላት በቴክኒክ፣ በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ማስታጠቅ የሚያስችሉ ሥራዎች እንዲሁም የሠራዊቱን ሕይወት ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፋችንን እጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል።