Search

በአፋር ክልል ጎሊና ወረዳ በጣለ ከባድ ዝናብ ከ500 በላይ ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 126

በአፋር ክልል ሀሪ ረሱ ዞን ጎሊና ወረዳ ከሉዋን ከተማ በጣለ ከባድ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ከ500 በላይ መኖሪያ ቤቶች ማውደሙን የወረዳው አስተዳደር አሊ ኢብራሂም ለኢቲቪ ተናግረዋል።

ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በቅርብ ጊዜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በአደጋው መጎዳቱን አቶ አሊ ኢብራሂም ተናግረዋል።

በዚህ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል።

በተጨማሪም የአርብቶ አደር ማህበረሰቡ ይጠቀምበት የነበረ የመጠጥ ውሃ ሶላር በአደጋው ከጥቅም ውጭ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ገልፀዋል።

በክልሉ በዘንድሮ ክረምት በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ንፋስ  የቀላቀለ ዝናብ መኖሪያ ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገልጿል።

የክልሉ መንግሥት በክረምት ወቅት ከባድ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ እያሰከተለ ያሚገኘውን ጉዳት ተከትሎ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በስፋት  እየሰራ ይገኛል ተብሏል

ሁሴን መሀመድ