ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በነበራቸው ጉብኝት ፓርኩ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጪያዎችን እያመረተ በመመልከታቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
በቬይትናም የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በነበራቸው ጉብኝት እና ከኩባንያው ፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው ውይይት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫዎችን በኢትዮጵያ ለማምረት ተስማምተው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።
በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የሚገኘው የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ማምረቻ በከፍተኛ ጥራት ከፍተኛ ምርት የማምረት አቅም የተላበሰ እና በዘመናዊ የማሽን ሥርዓት የሚሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ የምርት ውጤቱ ለማኑፋክቸሪንግ የውጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል ብለዋል።
ሁለት ተጨማሪ ማምረቻዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ እንደሆነ እና ወደ ምርት የገባውን ማምረቻ ሥራ ሂደት መመልከታቸውንም ጠቁመዋል።
ይህ ሥራ እሴት የተጨመረባቸው እና ያስቀመጥናቸውን ግቦች እና ፖሊሲዎች የሚያሳኩ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ከሚያደርገው የኢንቨስትመንት ስትራቴጂያችን ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #manufacturing #Hawassa