የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ማካሄድ ጀመረ።
ምክር ቤቱ በጉባኤ አዳራሹ እያካሄደ በሚገኘው በዚህ ስብሰባ፤ መጀመሪያ የስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔውን መርምሮ አጽድቋል።
በመቀጠልም ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: