የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ በ5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ባካሄደው የጠዋት መርሃ ግብሩ፣ የሁለት ቋሚ ኮሚቴዎችን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም መርምሮ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እና የሕገመንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡትን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመመርመርና በመወያየት አጽድቋል።
የምክር ቤቱ አባላት በሁለቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ በመመሥረት የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ የየቋሚ ኮሚቴዎቹ አመራሮችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የቀረቡት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲጸድቁ ለድምፅ ያቀረቡ ሲሆን፣ ምክር ቤቱም በሙሉ ድምፅ ደግፎ አጽድቋቸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: