ተቋሙ ከሃይል ሽያጭ እና ከተለያዩ ገቢዎች 63 ቢሊዮን በላይ ብር ገቢ መስብሰቡንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ተናግረዋል።
ዋናሥራ አስፈጻሚው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ከ8 ሺህ 350 ባላይ ከተሞች እና መንደሮች የአግልግሎቱ ተጠቃሚበማደርግ ሀገራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽንት 54 በመቶ ደርሷል ብለዋል።

አገልግሎቱ አሁን ላይ 5.2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በ2017 በጀት ዓመት በዋናው የሃይል ቋት እና ከዋናው የሃይል ቋት ውጭ 155 ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ማደረግ መቻሉ ገልጸዋል።
የሃይል ስርቆት ጋር በተያያዘ አንድ ሺህ የሚሆኑ ቆጣሪዎች መያዛቸውንበመግለጽ የሃይል መቆራረጥችግርን የጥገናእና የማስፋፊያ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ባለው ሥራ 94.8 በመቶ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያቸውን በዲጂታል መንገድ እንዲከፍሉ ማድረግ ተችሏል።
በ2018 አገልግሎቱ ከሃይል ሽያጭ 74 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት እና አጠቃላይ ገቢውን 101 ቢሊዮን ለማድረስ ማቀዱን ተናግረዋል።
አቤል ሙሉጌታ