Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፡-

ረቡዕ ሐምሌ 01, 2018 129

 

✅የዘንድሮው ምርጫ በተለያዩ ኃይሎች ምርጫው እንዳይካሄድ እገዳና ማስፈራሪያ ቢኖርም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ወደ ጎን በመተው በከፍተኛ ቁጥር በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠበት ታሪካዊ ክስተት ነው።

✅ሕዝቡ በምርጫው ጽንፈኝነትን፣ ዘረኝነትን እና መለያየትን እንደማይፈልግ በአንድነት አረጋግጧል። አረጋውያን፣ ሕሙማን እና ሐዘንተኞች ሳይቀሩ ለልጆቻቸው እና ለሀገር መጽናት ሲሉ በድጋፍ ወጥተው መርጠዋል።

✅ሕዝቡ ለመንግሥት የሰጠው ድምጽ "ባዶ ቼክ" ሲሆን፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን እንዲያስቀጥል፣ ስርአታዊ ሌብነት መጥፋቱን በመደገፍ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ትልቅ አደራ የጣለበት ነው። ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ፣ ጥይት ሳይፈራ የመረጠው ሕዝብ ነገ እርምጃ መውሰድ ይችላል።

✅የብልጽግና ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ፣ 15 በመቶ የሚሆነውን የምክር ቤት ወንበር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻቸውን እንዲወዳደሩበት አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይህም በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ዴሞክራሲያዊ እርምጃ ነው።

✅በሚቀጥለው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ብልጽግና ፓርቲ ከሚያቀርባቸው አጀንዳዎች አንዱ፣ በሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ መቆየት እንደሌለበት የሚደነግግ የሥልጣን ገደብ ሲሆን ይህም ለፖለቲካ ባህል ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው።

✅መንግሥት ከሕዝብ ጋር ባደረጋቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰፋፊ ውይይቶች ምክንያት፣ ብሔርን ከብሔር እንዲሁም ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ህዝባዊ ግጭቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል።

✅አሁን አልፎ አልፎ የሚታዩት ግጭቶች ሕዝብ ከሕዝብ የሚጋጭባቸው ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ ተረጋግታ እንዳትቀጥል በሚፈልጉ ኃይሎች እና በእነሱ ተላላኪዎች (ባንዳዎች) አነሳሽነት የሚፈጠሩ ናቸው።

✅የጸጥታ ተቋማት አቅማቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደጉ ቢሆንም፣ መንግሥት አሁንም ትጥቅ አንስተው ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በውይይት፣ በድርድር እና በምክክር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እውነተኛ ጥሪውን ያቀርባል። 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: