የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ባወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ዛሬ የዑለማ (የሃይማኖት ሊቃውንት) ምርጫ ተካሂዷል።
ኢቢሲ በተገኘበት በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 3 ሀምዛ መስጂድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ ድምፅ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንት አስቀድመው ለመራጭነት በተመዘገቡበት መስጂድ ተገኝተው ነው ድምፅ የሰጡት።
ዛሬ በዑለማ (በሃይማኖት ሊቃውንት) የተጀመረው ምርጫ በቀጣይ ሁለት ቀናት በወጣቶች፣ በሴቶች፣ በምሁራን እና በሠራተኛ ማሕበረሰብ ዘርፍ ይካሄዳል።
ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ል የተጀመረው የመጅሊስ ምርጫ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ል የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በማዋቀር እና መሪዎችን በመምረጥ ይጠናቀቃል።
የመራጭነት ምዝገባ የተመዘገቡ ሙስሊሞች በቀሪዎቹ ቀናት በተመዘገቡበት ዘርፍ በነቂስ ወጥተው ወኪሎቻቸውን እንዲመርጡም ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
#EBC #EBCdotstream #EIASC #election #scholars