Search

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ ተደራሽነት እና ሕዝባዊ መሠረት በአሃዞች

ዓርብ ሐምሌ 03, 2018 79

የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ለመወሰን እየተከናወነ ያለው ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ሂደት፣ ፍፁም ሕዝባዊ መሠረት ያለውና ሁሉንም ተደራሽ ያደረገ ለመሆኑ ወሳኝ ማሳያዎችን በአሃዞች ምን ይመስላሉ፦

በሂደቱ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች የተመረጡባቸው አጠቃላይ የወረዳዎች ብዛት 1,195 ሲሆን፣ በየወረዳው በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ደግሞ 10 ማኅበራዊ መሠረቶች ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።

ከእነዚህም መካከል የተወከሉትን ማኅበራዊ መሠረቶች በውይይቱ ላይ እንዲወክሉ 8,515 ሕዝባዊ ወኪሎች ተመርጠዋል።

በተጨማሪም ሥራዎችን ይበልጥ ለማቀላጠፍ በሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 15 የክልል ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን፣ ተአማኒነት ያላቸውን ወኪሎች በማስመረጥ ተግባር ላይ ደግሞ 7 ተባባሪ አጋር አካላት ኮሚሽኑን በቁርጠኝነት አግዘዋል።

ይህ ሰፊና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ፣ የምክክር መድረኩ እውነተኛ የሕዝብ ድምጽ እንዲሆንና ለዘላቂ ሀገራዊ መግባባት ጽኑ መሠረት እንዲጥል እያደረገው ይገኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: