Search

ታሪካዊ ቅርሶችን ከመታደግ እስከ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻነት የሐረር አስደናቂ የቱሪዝም ስኬት

ዓርብ ሐምሌ 03, 2018 57

መንግሥት ካስቀመጣቸው አምስት ቁልፍ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ጥንታዊ ውበቷን ከዘመናዊ ገጽታ ጋር በማሰናሰል አዲስ ገጽታን የተላበሰችው ሐረር፣ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የኮሪደር ልማትና የቅርሶች እድሳት ስራ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ አነቃቅታለች።

የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሀብት የሆኑት የሐረር ጀጎል ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲለሙና ለትውልድ እንዲተላለፉ ተደርጓል።

ይህ በዘርፉ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ለአደጋ ተጋርጠው የነበሩ ቅርሶችን ከማዳኑም ባሻገር፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋትና የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም በእጅጉ አሳድጎታል።

 

በበክልሉ የተከናወኑት ስኬታማ የቱሪዝም ማጎልበት ተግባራት፣ ከውጭ ሀገር ቱሪስቶች በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሐረርን በስፋት እንዲጎበኙና አስደናቂ ውበቷን ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።