Search

ከማዕድን ማውጫነት ወደ ቱሪዝም መንደርነት የተቀየረው የቻይና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ማሳያ

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 108

በቻይና ዠያንግ ግዛት የምትገኘው የዩኩን መንደር ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሆነው የኖራ ድንጋይ መገኛ ነበረች።

በዚህም ምክንያት በርካታ የማዕድን አውጪዎች በማሕበር በመደራጀት በመንደሯ የኖራ ድንጋይ እያመረቱ ወደ ፋብሪካዎች ይልኩ ነበር።

ነገር ግን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ማዕድን አውጪዎቹ በዚህ ሥራ የአካባቢው ስነ ምህዳር ምን ያህል እየተጎዳ እንዳለ አልተረዱም ነበር።

መንደሯ በአቧራ የተሸፈነች እና ለኑሮ እጅግ ከባድ እየሆነች በመምጣቷ ነዋሪዎቿ እና የአካባቢው አስተዳደሮች የአካባቢውን ማሕበረሰብ እንዴት ወደ ሌላ የቢዝነስ ዘርፍ እንደሚሰማሩ ተወያዩ።

በዚህም ድፍረት የተሞላበት ውሳኔን በጋራ ወሰኑ። የማዕድን ማውጣት ሥራን ማቆም እና የተራቆቱ ተራሮችን ችግኝ ማልበስመንደሯን ለም አቀፍ የቱሪስት ማዕከልነት  መቀየር የሚል ውጥን ይዘውም ሥራቸውን ጀመሩ።

ሥራቸው እጅግ አድካሚ ነበርለማዕድን ተብሎ የተቦረቦሩ ተራሮችን መንከባከብየደረቁ የውሃ አካላትን መመለስ እና የተራቆተውን የደን ሃብት መመለስ ጊዜ የሚወስድ ነበር።

ጥረታቸው ፍሬ ማፍራት ጀምሮ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በአካባቢው ለውጥ በመገረም የበፊት እና የአሁኑን ገጽታ በማሕበራዊ ሚዲያ በማጋራት  ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን መሳብ ጀመሩ።

የአካባቢው ነዋሪዎችም እየጨመረ የመጣው የቱሪስት ቁጥር የሥራ ዕድል ይዞላቸው መጣ።  ቤታቸውን ለቱሪስቶች ማረፊያነት በማዋል ሰፊ ጥቅም ማግኘት ጀመሩ።

ለአካባቢው አየር መበከል ምክንያት የነበሩት ፋብሪካዎች ዛሬ ላይ ወደ ካፌዎች እና  መዝናኛ ቦታዎች ሆነዋል የአየሩ መበከል ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ የነበረው ቦታ ዛሬ በአረንጓዴ እጽዋት በመሞላቱ የአለማችን ንጹሕ አየር ካለባቸው ስፍራዎች አንዱ ሆኗል።

እ.አ.አ. በ2024 ብቻ ዩኩን መንደር 1.2 ሚሊዮን ቱሪስቶች ተጎብኝቷል የመንደሯ ነዋሪዎች በፊት የማዕድን ማውጫ እያለ የሚያገኙት ገቢ አሁን ላይ 5 እጥፍ መጨመሩንም ሲጂቴን ዘግቧል።

ቻይና እንደ ሀገር በያዘችው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መርህ አምራች ያልሆኑ አካባቢዎችን ወደ ምርታማነት በመቀየር የዜጎች እና የሀገር ኢኮኖሚ በመለወጥ ላይ ትገኛለች።

 

 

በሃብተሚካኤል ክፍሉ

#EBC #ebcdotstream #Greenlegacy #China