የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአንከሬጅ አላስካ አየር ማረፊያ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።
በአየር ማረፊያው በርካታ የጦር ጀቶች የታዩ ሲሆን፣ ጥበቃውም ከበድ ያለ እንደሆነ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው።
በአላስካ አየር ማረፊያ በዘተጋጀላቸው ቀይ ምንጣፍ ላይ ሆነው እጅ ለእጅ ከተጨባበጡና የፎቶ ግራፍ መነሳት ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።
ከዚህም በኋላ ዓለም በጉጉት ወደሚጠብቀው ውይይት ያመሩ ሲሆን፤ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑም ተዘግቧል።
የልዑካን ቡድናቸው ይዘው ወደስብሰባው ስፍራ የገቡት ፕሬዚዳንቶቹ በዩክሬን ጉዳይ ላይ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#EBC #ebcdotstream #russia #usa