Search

ጥንቃቄ የሚሻው የክረምት የመሬት መንሸራተት አደጋ

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 126

በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ክረምቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የመሬት መንሸራተት ለመቀነስ እና ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለሙያ በመመደብ የክረምት መሬት መንሸራተት አደጋ ስጋት ባለባቸው ቦታዎች የቅድመ ክትትል እና የጥንቃቄ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ኦፕሬሽን ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፍራኦል በቀለ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ የሚያደርግ በመሆኑ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑን አመላክተዋል።

ባለፈው ዓመት በጎፋ አካባቢ በተደረገው ጥናት አካባቢው ለአደጋ አስጊ በመሆኑ ከ 16 ሺህ በላይ ሰዎችን ከአካባቢው በማራቅ መሰረተ ልማት ወደተሟላለት አካባቢ ማዘዋወር ተችሏል ሲሉ አስታውሰዋል።

እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢ ተመሳሳይ የአደጋ ስጋት በሚከሰትበት ወቅት ቅድመ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ በአፋር ክልል በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ80 ሺህ በላይ ሕዝብን ከስጋት አካባቢው ማራቅ እንደተቻለ ገልፀዋል።

ማህበረሰቡ የአደጋ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ሕይወቱን እንዳይመሰርት በሚደረገው ስራ ላይ ተባባሪ እንዲሆን እና በተገቢው መንገድ እንዲተገብር መክረዋል።

 

በሄለን ተስፋዬ

#EBC #ebcdotstream #landslide