Search

ኢትዮጵያ በቀኝ በግራ እየተሰራች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 10, 2017 218

ኢትዮጵያ በቀኝ በግራ እየተሰራች የማንሰራራት ዘመኗ የሚታይ የሚጨበጥ ሆኗል ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎችን እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት፤ ኢትዮጵያ እየተሰራችና እያንሰራራች ያለችበትን ሂደት ያልተገለጠላቸው አካላት በሂደት ይገለጥላቸዋል ብለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ንፁህ እና ነዋሪዎቿም ከተማዋን ጠብቀው የሚኖሩባት ከተማ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም ትልቅ ተስፋ እንዲኖርን አድርጎናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ያማረ ተራራ፣ ያማረ ጫካ እና ውሀ ተሰናስሎ የሚታይበትን ይህን ስፍራ፤ ማስተካከል እና ማስዋብ ከተቻል አርባምንጭ ካሉን ምርጥ ቦታዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አርባ ምንጭ፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ድሬድዋ ላይ የሚታየው ነገር ከአዲስ አበባ ውጭ አማራጭ ቦታዎች እየሰፉ እንደሚገኝ ያመላክታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በሀገራችን ያሉንን ቦታዎች ማልማት ከቻልን የትም ቦታ ሄደን ምርጥ ነገር መመልከት እንችላለን ሲሉም አክለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩት ነገሮች የራሳቸው ውበት አላቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን በማልማት ለልጆቻችን ማረፊያ፣ መዋያ፣ ገንዘብ ማምጫ፣ ማሰቢያና ማሰላሰያ ስፍራን መፍጠር እንችላልን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በሐይማኖት ከበደ

#ebc #ebcdotstream #PMOEthiopia #PMAbiy #arbaminch