Search

መከራን ወደ ዕድል በመቀየር ለትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን እናውርስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ሐምሌ 08, 2018 83

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን ፈተናዎች ወደ ዘላቂ መፍትሄና ዕድል በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እንደገለጹት፣ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ማዕበሎች ወይም መከራዎች በውስጣቸው ዕድልን አዝለው ይገኛሉ።

መከራ ሁሉ መከራ ብቻ ሳይሆን በውስጡ ዕድል አለው፤ ችግር ሁሉ ችግር ብቻ ሳይሆን በውስጡ መፍትሄ ያለው ማለት ነውያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን የፈተና ጊዜ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ለልጆች በተሻለ ሰላምና ብልጽግና የምትኖር አገር መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (/) አያይዘውም፣ዕድሎች የሚበዙለትና የሚበራከቱት በሚጠቀምባቸው ሰው ልክ ነውበማለት የዕድል አጠቃቀምን አስፈላጊነት አብራርተዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገኙ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የወታደራዊ ሪፎርም ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለይም አዲስ አበባ ከተማን የቆሸሸ ገጽታ በመቀየር ዘመናዊና ውብ እንዲትሆን የተደረገው ጥረት የዕድል አጠቃቀም ውጤት መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የምናገኛትን እያንዳንዱን ደቂቃ እንደ ታላቅ ስጦታ በመቁጠር፣ የኢትዮጵያን የብልጽግና መሰረት ለመጣል ደከመን ሰለቸን ሳይሉ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

አሁን ያለው ትውልድ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በአግባቡ በመጠቀም፣ ለልጆች የተዋበ የኑሮ ዘይቤ መፍጠር እንደሚጠበቅበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  በንግግራቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።

በጌቱ ላቀው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: