Search

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ከማል በድሪ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ረቡዕ ሐምሌ 08, 2018 374

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ1988 እስከ 2000 ዓ.ም ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አቶ ከማል በድሪ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሥርዓተ ቀብራቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃፊዎች በተገኙበት ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ከማል በድሪ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልፆ፤ ለቤተሰባቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: