የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የኮፕ 21 ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሎረን ፋቢየስ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ ለኮፕ 32 በሚደረጉ ዝግጅቶች፣ ጉባኤውን ስኬታማ ለማድረግ አስተዋጽኦ በሚኖራቸው ጉዳዮችና ካለፉት የኮፕ ጉባኤዎች በተገኙ ትምህርቶች ላይ ትኩረት አድርጓል።
በውይይቱ፣ ሎረን ፋቢየስ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ ታላቅ ስኬት የተመዘገበበትን የፓሪስ ስምምነት በማጽደቅ የተጠናቀቀውን ኮፕ 21ን የመሩበትን ልምድ አካፍለዋል።
ዶ/ር ጌዲዮን በበኩላቸው፣ የፓሪሱ ስምምነት ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃዎች ያለውን ዘላቂ ጠቀሜታ ገልጸዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቋቋም፣ የተገቡ ቃሎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር የመቀየርን አስፈላጊነት በአፅንዖት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ላይ እምነትን የሚያጠናክር ግልጽ፣ አካታች እና በአባል ሀገራት የሚመራ የኮፕ 32 ሂደትን ለመተግበር ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በዝግጅት ረገድም፥ ይዘትና ድርድር፣ ሎጂስቲክስና ኦፕሬሽን፣ አጋርነት እንዲሁም ሚዲያና ኮሙኒኬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችን አብራርተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: