Search

ለታላቁ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መሠረት የሆኑ እና በከፍተኛ ጥንቃቄና በባለሙያ ታግዘው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

ረቡዕ ሐምሌ 08, 2018 68

የአሠራር ሥርዓቶችን መዘርጋት፡- የምክክር ሂደቱ ህጋዊነትና ተዓማንነትን የጠበቀ እንዲሆን ግልጽነት፣ ተጠያቂነት ያላቸው የአሠራር መመሪያዎችና ሥርዓቶች ተዘርግተው  ተግባራዊ ተደርገዋል።

የምክክር ሂደት ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ፡- የምክክር ሂደቱ አካታችና ፍትሃዊ እንዲሆን ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አርሶና አርብቶ አደሮችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ተቋማትና ማኅበራትን፣ ምሁራንና የማኅበረሰብ መሪዎችን ያካተቱ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ በታማኝነትና በገለልተኝነት ተከናውኗል።

አጀንዳ የማሰባሰብና የመቅረጽ ሂደት፡- የሕዝቡን እውነተኛ ድምጽና የችግሮቹን ምንጭ ለመለየት በየደረጃው ሰፊ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራዎች ተካሂደዋል። እነዚህ የተሰበሰቡ ሃሳቦች በምሁራንና በባለሙያዎች ታግዘውና በባለድርሻ አካላት ግብአት ተሰጥቶባቸው ለምክክሩ በሚያመች መልኩ ተቀርጸው ተዘጋጅተዋል።

ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች፡- ኅብረተሰቡ ስለ ሀገራዊ ምክክሩ ምንነት፣ አስፈላጊነትና ግብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረውና የሂደቱ ባለቤት መሆኑን እንዲረዳ ሰፊ የማንቃትና የማስተማር ሥራዎች በመላው ኢትዮጵያ ተከናውነዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: