Search

በፓኪስታን በደረሰው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 321 ደረሰ

ቅዳሜ ነሐሴ 10, 2017 121

በፓኪስታን ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 321 መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በአደጋው አብዛኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በፓክቱንዋ ግዛት ሲሆን 307 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

በካሽሚር እና ባልቲስታን ግዛቶች ተጨማሪ የሞት አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን ከባድ ዝናብ አሁንም እየዘነበ በመሆኑ በአካባቢው ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በተለምዶ ከሰኔ እስከ መስከረም የሚዘልቀው ፓኪስታንን ጨምሮ በደቡብ እስያ የሚዘንበው ዝናብ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በቅርብ አመታት ውስጥ አውዳሚ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎችን እያስከተለ ይገኛል።

የፓኪስታን የነፍስ አድን ሰራተኞች ስጋት ውስጥ ያሉ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ስፍራዎች የማዘዋወር ስራ በመስራት ላይ ናቸው ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#ebc #ebcdotstream #Pakistan #flood #landslide