የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ ሊገናኙ መሆኑን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አረጋግጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ እንዳስታወቁት ሰኞ ጦርነቱን ስለማስቆም እና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ወደ አሜሪካ እንደሚያቀኑ እና እንደሚወያዩ ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕን ላደረጉላቸው ጥሪ ያመሰገኑት ዘለንስኪ፤ ዩክሬን ደም አፋሳሹን ጦርነት ለማስቆም ቁርጠኛ ናት ያሉ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ያደረጉትን ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች ማወቃቸውንም ገልጸዋል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ፊት ለፊት ቀርባ ለመነጋገር እና በመሪዎች ደረጃ መደራደርን እንደ መርህ እንደምትይዝ እና የአውሮፓ ሀገራት ተሳትፎን እንደአስፈላጊነቱ እንዲኖር እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
ትራምፕ እና ዘለንስኪ ከዚህ በፊት በዋሽንግተን በነበራቸው ስብሰባ ሳይስማሙ እንደተለያዩ የአናዶሉ ዘገባ አስታውሷል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #ebcdotstream #Usa #Ukraine