Search

የጭስ አልባ ትራንስፖርት ዘርፍን ለማስፋፋት ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ተስማምተናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዓርብ ሐምሌ 10, 2018 70

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና በተለይም የጭስ አልባ ትራንስፖርት (E-mobility) ተደራሽነትን በስፋት ለማዳረስ እያከናወነ ባለው ሥራ ዙሪያ በዝርዝር መምከራቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በውይይታቸውም አስተዳደሩ የጀመራቸውን ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር፣ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ የግል ተቋማትን ለመደገፍ ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት እና በትብብር በጋራ ለመሥራት ተግባብተናል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች ለዳይሬክተሯ ማርያም ሳሊም እና አብረዋቸው ለነበሩት የቴክኒካል ቡድን አባላት በራሳቸው እና በአዲስ አበባ ሕዝብ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: