Search

የነገው ሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

ዓርብ ሐምሌ 10, 2018 122

በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መልዕክት ለማስተላለፍአፈሳ ይቁም፣ ሰላም ይስፈንበሚል መሪ ቃል ነገ ሐምሌ 11 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል።

በመሆኑም ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ፣

 ከመገናኛ 22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ዑራኤል አደባባይ ላይ፣

 በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ላይ፣

 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ለገሀር መብራት ላይ፣

 ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲየም፣ ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ላይ፣

 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ላይ፣

 ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ፣ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ፣

 ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ፣ ሐራምቤ መብራት ላይ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በተጨማሪም ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 . ከምሽቱ 1200 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው ገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: