ወላይታ ሶዶ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ጽኑ አቋማችን ምስክር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ከአርባምንጭ እስከ ወላይታ ስንጓዝ የአረንጓዴ ልማት ሥራችን ውጤት እንዲሁም አስደናቂ የፍራፍሬ እርሻ ልማት መስክ ተመልክተናል ብለዋል።
እነዚህ ጥረቶች የመልከዓ ምድሩን ልምላሜ ከመመለስ ባሻገር የአኗኗር ዘይቤንም የማሸጋገር ሥራዎች ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት።
በጠንካራ የሥራ ባሕሉ እና ኅብረቱ የሚታወቀው የወላይታ ሕዝብ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ጠንካራ ሚና መወጣቱን ቀጥሏል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
#EBC #EBCdotstream #WolaitaSodo #PMAbiyAhmed