Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ሰጡ

እሑድ ሐምሌ 12, 2018 131

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 2018 በጀት ዓመት የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በመሥራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ዕውቅናና ሽልማት አበርክተዋል።

በዚሁም መሰረት፦

የካቢኔ አባል ከሆኑ ቢሮዎች፦(መኪና ተሸላሚዎች)

1. ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

2. ጤና ቢሮ

3. ገቢዎች ቢሮ እና ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

4.  ትምህርት ቢሮ

5. ልዩ ተሸላሚ የሆነው :-ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል

ከክፍለ ከተሞች፦ (መኪና ተሸላሚዎች)

1. ቦሌ ክፍለ ከተማ

2. ለሚኩራ ክፍለ ከተማ

3. አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ

የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት፦ (መኪና ተሸላሚዎች)

1. ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

2. መንገዶች ባለስልጣን

3. ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

4. አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን

5. ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆን

በተጨማሪም 33 ወረዳዎች፣ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከእያንዳንዱ ወረዳ ከአንድ እስከ ሶስት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ተሸላሚ ሆነዋል።

 የካቢኔ አባል ከሆኑ ቢሮዎች፦የሰርተፍኬት ተሸላሚዎች

1. ፋይናንስ ቢሮ

2. ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

3. ኮሙኒኬሽን ቢሮ

4. ንግድ ቢሮና

5. ፍትሕ ቢሮ

የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት፦(የሰርተፍኬት ተሸላሚዎች)

1. ሲቪል ምዝገባና  የነዋሪነት አገልግሎት

2. የመስሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር

3. አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

 ከክፍለ ከተሞች:-

(የሰርተፍኬት ተሸላሚዎች)

1. ኮልፌ ክፍለ ከተማ

2. ልደታ ክፍለ ከተማና የካ ክፍለ ከተማ ናቸው።

"ዛሬ የተሰጠነው እውቅናና ሽልማት የሁሉም አመራር፣ በየደረጃው ያሉ ባለሞያዎች፣ የባለድርሻ አካላት እና አብሮን ለሰራው ህዝባችን ለጋራ የቅንጅት ስራ  የተሰጠ ሲሆን ይህም  ይበልጥ ሰርተን የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት የምናሳካበት፣ የውድድር መንፈስን የምንፈጥርበት፣ ወደኋላ የቀሩት ራሳቸውን ፈትሸው ወደፊት የሚመጡበት እንጂ የሚያዘናጋን አይደለም።

 በመሆኑም፤ እውቅናው በቀጣይ በጀት ዓመት አልቀን በመስራት የህዝባችንን ተጠቃሚነት እንድናረጋግጥ፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን አልቀን እንድንሰራ ከትልቅ አደራም ጭምር ነው።"

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: