የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በዘንድሮው የክረምት ወራት የሚያከናውናቸውን ዘርፈ ብዙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች በይፋ አስጀምሯል።
መርሐ ግብሩን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር በጋራ አስጀምረውታል።
ኮርፖሬሽኑ በበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን ያካተተ ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚሆኑ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታ፣ የችግኝ ተከላ፣ የጤና መድህን ሽፋን እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ይገኙበታል።
በተለይም በከተማው ወረዳ 6 አካባቢ በይፋ የተጀመሩት የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ግንባታ አስፈላጊውን መሠረታዊ አገልግሎት አሟልተው በጥራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉ ተገልጿል።
ከዚህ ግንባታ ጎን ለጎንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለመቶ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የሚሆን የዓመታዊ ጤና መድህን ዋስትና ሽፋን የገንዘብ ድጋፍ እና ለተማሪዎች የሚውሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር አስረክበዋል።
በማስጀመሪያ ስነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ረሻድ ከማል፣ በአገራዊ ለውጡ ማግስት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብሮች አሁን ላይ ጠንካራ የአገር ባህል እየሆኑ መምጣታቸውን አስገንዝበዋል።
አክለውም አረንጓዴ አሻራ ከድህነት መውጫ ቁልፍ መንገድ መሆኑን ጠቁመው፣ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራት ደግሞ የኢኮኖሚ ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው በድሬዳዋ ቆይታቸው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: