ቴክኖሎጂ እና ኢንተርኔት ዓለማችንን አንድ ትንሽ መንደር እያደረጓት መሆኑን ቻይናውያን በተግባር እያረጋገጡልን ነው። ባለንበት የ2026 ዓ.ም ብቻ 140 ሚሊዮን የሚሆኑ ቻይናውያን ድንበር ተሻጋሪ የኢ-ኮሜርስ (Cross-border E-commerce) መድረኮችን በመጠቀም የኦንላይን ግብይት መፈጸማቸውን ሰምታችኋል?
ይህ ማለት ቁጥራቸው ከበርካታ ሀገራት ጠቅላላ የህዝብ ብዛት የሚበልጥ ሰዎች ቤታቸው ቁጭ ብለው ከሌላ አለም እቃ ገዝተዋል፤ የራሳቸውንም ሸጠዋል ማለት ነው።
ይህ አስገራሚ የኦንላይን ሸመታ ማዕበል ዝም ብሎ በአጋጣሚ የተፈጠረ አይደለም። ዘመናዊ እና ፈጣን የዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች፣ እቃን በቅጽበት የሚያደርሱ ፈጣን የሎጂስቲክስ አውታሮች፣ ግዙፍ የመጋዘን አቅም እና ምቹ የሆኑ የመንግስት ፖሊሲዎች የገበያውን ድባብ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።
አስቡት... ከየትኛውም የዓለም ጥግ የተመረተን ምርጥ እቃ በስልካችሁ ማዘዝ እና በፍጥነት እጃችሁ ላይ መግባት ሲችል ምን ያህል ደስ ይላል? የቻይና የኢ-ኮሜርስ መድረኮች ይህንን በማቅለል የውጭ ምርቶች ወደ ቻይናም ሆነ የቻይና ምርቶች ወደ ተቀረው ዓለም በቀላሉ እንዲደርሱ ድልድይ ሆነዋል።
የህዝቡ የዲጂታል አጠቃቀም ባህል እያደገ መምጣቱ ደግሞ ገበያውን ይበልጥ አድምቆታል። ከዚህ ግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴ ጀርባ ቻይና በዓለም የዲጂታል ንግድ መሪ ሀገራት መካከል ያላትን ስፍራ ይበልጥ እያጠናከረች መሆኑን ያሳያል።
በቀጣይም በቴክኖሎጂ፣ በሎጂስቲክስ እና በዓለም አቀፍ ትብብር በሚደረጉ አዳዲስ ማሻሻያዎች ይህ የድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ እድገት የበለጠ ፈጣን እና አስገራሚ እንደሚሆን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
ለመሆኑ እናንተ በኦንላይን እቃ ገዝታችሁ ታውቃላችሁ? የትኛውን መተግበሪያስ ትጠቀማላችሁ? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን።
በቃልኪዳን ማዕድን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: