በጋምቤላ ክልል አዲስ አመራሮች ወደ ስልጣን የመጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ እና የተጀመሩ የሰላምና የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ላይ ያተኮረ የእግር ጉዞ ተካሂዷል።
በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በክልሉ በመንግሥት እና በማኀበረሰቡ ተሳትፎ የተገኘው ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል የአብሮነት እና የወንድማማችነት እሴቶችን ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በክልሉ የተገኘው ሰላም ሳይደናቀፍ እንዲቀጥል ማኀበረሰቡ ከምን ጊዜውም በላይ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አመላክተዋል።
ሰላምን በማደፍረስ የሕዝቦች አብሮት እንዲሸረሸር የሚፈልጉ አካላትን ማኀበረሰቡ በማጋለጥ እኩይ ተግባራትን መግታት እንደሚገባዉም ርዕሰ መስተዳድሯ ተናግረዋል።
በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በመጠቀም የምግብ ሉኣላዊነትን ለማረጋገጥ እና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ሥራዎችን በስፋት እየተከናወኑ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሯ አስረድተዋል።
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የክልሉ ሰላም እና የልማት ጉዞ ጠንካራ መሰረት እንዲኖረው ማኀበረሰቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ኃላፊነቱን ከምን ጊዜውም በላይ ሊያጠናክር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
አዳዲስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የኢቢሲን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር እና ፕለይ ስቶር አውርደው ዲጂታል ኢቢሲን ይቀላቀሉ።
አንድሮይድ (Android) ስልክ የምትጠቀሙ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/6KegY
አይኦኤስ (iOS) ስልክ የምትጠቀሙ ደግሞ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/hFuA1