Search

ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገርን ለማፍረስ እየሠራ ያለው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ሊወገዝ ይገባል - አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ

ሓሙስ ሐምሌ 16, 2018 126

መላው ኢትዮጵያውያን ሀገርን በምክክር ለማጽናት ተሰባስበው እየመከሩ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገርን ለማፍረስ እየሠራ ያለው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን በሁሉም ሊወገዝ እንደሚገባ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን በመወከል በምክክር ጉባኤው እየተመካከሩ የሚገኙት ተስፋሁን ዓለምነህ ተናገሩ።

አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ፣ የምክክር ኮሚሽኑ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቡን አንሥተው፣ አሁንም ይህንን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ጦርነትን የሚሰብኩ አካላትን የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ መላው ሕዝብ ሊያወግዛቸው ይገባል ብለዋል።

ልዩነትን በጠመንጃ ለመፍታት የተሄደበት ጉዞ ኢትዮጵያን በብዙ የጎዳ እና ያከሰረ መሆኑን ገልጸው፣አሁን በዚህ ዘመን ጠብመንጃ በፍጹም አማራጭ ሊሆን አይችልም፤ አዲስ የምክክር ምዕራፍ ተከፍቷልሲሉ ተናግረዋል።

ሀገር ሰላም ስትሆን ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ይኖራታል፤ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚፈልጉትን ማሳካት እንዳይችሉ ስለሚያደርጋቸው ሀገርን ለማተራመስ እና እርስ በርስ ለመከፋፈል እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ነገር ግን መላው ኢትዮጵያውያን አለመግባባትን በምክክር ብቻ በመፍታት ይህ ዓላማቸው እንዲከሽፍ በጋራ መቆም አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ ወጡን እና የሕዝብ ጠላት የሆነውን የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ በፍጹም አይፈልገውም፤ ሁሉም በጋራ ሊያወግዘው ይገባል በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በመስከረም ቸርነት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: